በአዲሱ የጡረታ አዋጅ (1268/2014) መሰረት የተለያዩ መመሪያዎች ጸደቁ፡፡

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተዳደር በቦርድ የፀደቀ የጡረታ ሥራ አፈፃፀም መመሪያ መመሪያ ቁጥር 01/2014 እንዲሁም በፕሮቪደንት ፈንድ ወይንም በሌላ ስያሜ በሚጠራ ዐቅድ ተጠቃሚ የነበሩ የግል ድርጅት ሠራተኞች በጡረታ ዐቅዱ የሚሸፈኑበት መመሪያ መመሪያ ቁጥር 02/2014 ፀደቁ፡፡