ሠራተኞችን ለማስመዝገብ መሟላት ያለባቸዉ ማስረጃዎች

  • በድርጅቱ ሲቀጠሩ የተሰጣቸው የቅጥር ደብዳቤ፣/ደመወዝ የሚገልጽ/ በተጨማሪምሰራተኛው አሁን ያለበት የደመወዝ ሁኔታ መገለጽ አለበት
  • በድርጅቱ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም የተሞላ የሕይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም ተብሎ በደብዳቤ ይገለፅ
  • የሠራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ አንደኛው ከጀርባው አንደኛው ከፊት ለፊት  የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት፣
    • ቀድሞ በመንግስት መ/ቤት የተፈጸመ አገልግሎት ካለ ካገለገሉበት መ/ቤት የቅጥር፣ የህይወት ታሪክ ፎርም እና የስንብት ደብዳቤ አገልግሎቱ ከ – እስከ በሚል ተገልፆ በድርጅቱ አድራሻ መቅረብ ይኖርበታል
    • በተመሳሳይ በጡረታ ዐቅድ በተሸፈነ የግል ድርጅት ውስጥ ያገለገበት ማስረጃ  ካለ መቅረብ አለበት
    • የሚስት/የባል አንድ ፎቶ ግራፍ የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት
    • የጋብቻ ማስረጃ ፣ ዕድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች የሆነ የልጆች የልደት ሠርተፊኬት መቅረብ አለበት
    • የሰራተኛው እናት በህይወት ቢኖሩም ባይኖሩም ስማቸዉ በቅጹ ፎርማት ላይ መገለጽ አለበት፡፡
    • የምዝገባ ማሳወቂያ ቅፅ(ቅፅ ግ.ድ ጡ1.1) ፎርሙን የሞሉ ሰራተኞች ስም ዝርዝር በሁለት ኮፒ ተሞልቶ ይቀርባል፡

ማሳሰቢያ

ቅጽ1/አንድ/ የሚሞላው  አንድ ጊዜ ብቻ ነው /ከአንድ ድርጅት ወደሌላ ሲቀይሩ ለተቀጠሩበት ድርጅት የተሰጣቸውን ቁጥር ማሳወቅ እና መቀጠራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ መምጣት ይኖርበታል፡፡

  • በስራ ላይ አደጋ ካጋጠመ የአስተዳደሩን የአደጋ ማሳወቂያ ቅፅ በመሙላትና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር በመግለፅ በ30 ቀናት ዉስጥ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
  • የሰራተኛዉም ሆነ አሰሪ ድርጅቱ ማንኛዉም የማስረጃ ለዉጥ ሲኖር የማህበራዊ ዋስትና መለያ ቁጥር በመግለፅ ለዉጡን በ60 ቀናት ዉስጥ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

በህመም የጡረታ አበል ጥያቄ ሲቀርብ መሟላት ያለባቸው ማስረጃዎች

1.መጀመሪያ ሲቀጠሩ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ፣ የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ) ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይጻፍ

  1. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት፡፡
  2. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  3. የአገልግሎት ጡረታ፣ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  4. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  5. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  6. ደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ
  7. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት
  8. 37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  9. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ አለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  10. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል
  11. ወር ሳይሞላ ለተሰናበቱ የተከፈለ ጉርድ ደመወዝ ካለ በመሸኛ ደብዳቤ ላይ መጠኑና የስንብት ቀኑ መገለጽ አለበት፡፡
  12. የሐኪሞች ቦርድ በህክምና ለማንኛውም ስራ ብቁ አይደሉም ብሎ ውሳኔ የሰጠበት ማስረጃ

     ለተተኪዎች የጡረታ አበል ጥያቄ ሲቀርብ

  1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ).ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይጻፍ
  2. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት ፡፡
  3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  4. የአገልግሎት ጡረታ፣ ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  7. ደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ
  8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት 9.  37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  9. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ አለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  10. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል
  11. ወር ሳይሞላ ለተሰናበተ የተከፈለ ጉርድ ደመወዝ ካለ በመሸኛ ደብዳቤ መጠኑና የስንብት ቀኑ መገለጽ አለበት፡፡
  12. የፍርድቤት ውሳኔ የተሰጠበት ማስረጃ፣
  13. ከ18 ዓመት በታች እና ከ 21 ዓመት በታች ለሆኑ የአካል ጉዳተኛ  ልጆች የልደት ሰርተፍኬት መቅረብ አለበት
  14. የተተኪዎች ሁለት ሁለት ፎቶግራፍ ጀርባዉ ላይ ጉዳዩን ያየው ፍርድ ቤት ማህተም

የጡረታ መዋጮ  መክፈያ ጊዜ

እያንዳንዱ የግል ድርጅት የሠራተኞቹን የጡረታ መዋጮ ከደመወዛቸው ቀንሶና የራሱን መዋጮ ጨምሮ ለጡረታ ፈንዱ በየወሩ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

ከሠራተኞቹ ደመወዝ ሊቀነስ የሚገባውን መዋጮ ሳይቀንስ የቀረ የግል ድርጅት በአዋጁ አንቀፅ ፲፪ ንዑስ አንቀፅ ፫መሰረት ክፍያዉን ራሱ ለመፈጸም ኃላፊ ይሆናል፡፡

የጡረታ መዋጮ ለሠራተኞች የወር ደመወዝ ከሚከፈልበት ወር መጨረሻ ቀን አንስቶ በ ፴ ቀናት ውስጥ ለጡረታ ፈንዱ ገቢ መደረግ አለበት፡፡

ገቢ የተደረገበት የሰራተኞች የጡረታ መዋጮ ገቢ ማሳወቂያና ገቢ የተደረገበት ደረሰኝ በኢ-ታክስ ወይም በሃርድ ኮፒ ለገቢ ፅ/ቤት እንደአስፈጊነቱ ለአስተዳደሩ  ቅ/ፅ/ቤቶች ማሳወቅ አለበት፡፡

በዕድሜ የጡረታ አበል ለማስከበር መሟላት ያለባቸው ማስረጃዎች

  1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ).ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይፃፍ
  2. የቅጥር ና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት ፡፡
  3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  4. የአገልግሎት ጡረታ፣ ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  7. የደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ መያያዝ አለበት
  8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት
  9. የ37ኛው ወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  10. የድርጅት መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል መላክ ይኖርበታል፡፡ ( ከዚህ በፈት ከተላከ መላኩ ይገለፅ  )
  11. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ አለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  12. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል

በራስ ፍቃድ የጡረታ አበል ሲጠየቅ መሟላት ያለባቸው ማስረጃዎች

  1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም (የስራ መጠየቂያ)፣ የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ). ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይጻፍ
  2. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት ፡፡
  3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  4. የአገልግሎት ጡረታ፣ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  7. የደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ መያያዝ አለበት
  8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት
  9. 37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  10. የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል መላክ ይኖርበታል፡፡ ( ከዚህ በፊት ከተላከ መላኩ ይገለፅ
  11. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ አለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  12. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል
  13. ባለመብቱ/ቷ በራሳቸው ፍቃድ ስራ ለማቋረጥ የጠየቁበት ማመልከቻ እንዲሁም ድርጅቱ ጥያቄውን የተቀበለበት የስንብት ደብዳቤ

በጉዳት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየ ሰው የጡረታ አበል ሲጠየቅ መሟላትያለባቸዉ ማስረጃዎች

  1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ፣ የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ). ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይፃፍ
  2. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት፡፡
  3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  4. የአገልግሎት ጡረታ ፣ ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  7. የደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ መያያዝ አለበት
  8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት
  9. 37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  10. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ አለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  11. የፖሊስ አደጋ ሪፖርት፣ የጉዳት ማሳወቂያ ቅጽ ግ.ድ ጡ-1.3 ተሞልቶ መቅረብ አለበት

12 የአስክሬን ምርመራ ውጤት

  1. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል፡፡

የጉዳት ዳረጎት አበል ጥያቄ ሲቀርብ

  1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ).ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይጻፍ
  2. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት፡፡
  3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት
  4. የአገልግሎት ጡረታ፣ ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት
  5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት
  6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት
  7. የደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ መያያዝ አለበት
  8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት
  9. 37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት
  10. የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል መላክ ይኖርበታል፡፡ ( ከዚህ በፊት ከተላከ መላኩ ይገለፅ )
  11. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ ስላለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ
  12. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል
  13. የጉዳት ማሳወቂያ ቅጽ ግ/ድ/ጡ/1.3 ተሞልቶ መቅረብ አለበት
  14. እንደየሁኔታው የፖሊስ ሪፖርት(የመኪና አደጋ ሲሆን)
  15. በህክምና ቦርድ የተረጋገጠ የህክምና የጉዳት መጠን ማስረጃ