ከግል ድርጅት መመዝገቢያ ቅጽ ጋርያይዘው መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች

  • ለL.C /ኃላ/የተ/የግ/ማ/ የሽርክናማኅበርወይም ለshare company ንግድ ፈቃድ፣ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ ፣ቲን ሰርተፍኬት፣ የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል ፎቶ ኮፒ በሁሉም  ማስረጃ  ላይ ማህተም ተደርጎበት በሸኚ ደብዳቤ እና የሰራተኞችን መመዝገቢያ ቅፅ በሶፍት ኮፒ ለመዉሰድ ባዶ ሲዲ አብሮ መቅረብ አለበት
  • L.C ላልሆኑ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፍኬት የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል  ፎቶ ኮፒ በሁሉም ማስረጃ  ማህተም ተደርጎበት በሸኚ ደብዳቤ እና የሰራተኞችን መመዝገቢያ ቅፅ በሶፍት ኮፒ ለመዉሰድ ባዶ ሲዲ አብሮ መቅረብ አለበት
  • መንግሥታዊ ላልሆኑ(NGO)  ድርጅቶች፡- ቲን ሰርተፍኬት፣  የምዝገባ ፈቃድ የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል  ፎቶ ኮፒ በሁሉም  ማስረጃ  ማህተም ተደርጎበት   በሸኚ ደብዳቤ እና የሰራተኞችን መመዝገቢያ ቅፅ በሶፍት ኮፒ ለመዉሰድ ባዶ ሲዲ  አብሮ መቅረብ አለበት

ማሳሰቢያ፡

  1. ማንኛውም የምዝገባ ፎርም ይዞ የሚመጣ ሰው የመ/ቤቱን ውክልና እና የመ/ቤቱን ማህተም ይዞ መምጣት አለበት፡፡
  2. የድርጅት መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል ከሌለ አለመኖሩ በደብዳቤ መገለፅ  ይኖርበታል::

      በጡረታ ዐቅዱ የማይሸፈኑ

  • እድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግል ድርጅት ሠራተኞች፤
  • መንግስታዊ አለም አቀፍ ድርጅቶችና የውጭ መንግስታት ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ሠራተኞች፣
  • የቤት ሰራተኞች
  • በስማቸው ድርጅት ከፍተው የሚያሠሩ የስራ መሪዎች ወይም ሠራተኞች ወይም የግል ድርጅት ባለቤቶች፤
  • የዉጭ ሀገር ዜጎች

በጡረታ ዐቅዱ የሚሸፈኑ

  • በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ የግል ድርጅት ሠራተኞች በሙሉ

በጡረታ ዐቅዱ በፍቃደኝነት የሚሸፈኑ

  • የሃይማኖት ድርጅቶችና ሠራተኞች፤
  • የፖለቲካ ድርጅቶችና ሠራተኞች፣
  • መደበኛ ባልሆነው የስራ መስክ ላይ ተሰማርተው ያሉ