ማስታወቂያ

ለግል ድርጅቶች በሙሉ

በአዋጅ ቁ.1268/2014 ላይ እንደተደነገገው የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ፣ወለድና ቅጣት የሚሰበሰበው በፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴርና በክልሎች ገቢዎች ቢሮ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ታክስ የሚሰበሰበው በኢ-ታክስ በመሆኑ በዚሁ የኢሌክትሮኒክስ የታክስ አሰባሰብ በሚደረግባቸው ቦታዎች ሁሉ ክፍያ የምትፈፅሙ የግል ድርጅቶች የጡረታ መዋጮ ገቢ ክፍያ በኢ-ታክስ ስትፈፅሙ፣ክፍያ የተፈፀመላቸውን ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ ከታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በኢ-ታክስ የክፍያ ሲስተም እንድታሳውቁን እናሳስባለን፡፡

               የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር