የዋና ሥራ አስፈጻሚ መልዕክት
የማኅበራዊ ዋስትና/social insurance/ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለዉ በጀርመን ሀገር እ.ኤ.አ. ከ1883-1889 ነው፡፡ምክንያቶቹም የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት፣ በሠራተኞች ላይ የጉዳት መበራከት፣ የተፈጠረዉ ርካሽ ጉልበት ደመወዝን ዝቅተኛ በማድረጉ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ዝቅተኛ ደመወዝ መከፈሉ ናቸው፤ሠራተኛው ከእጅ ወደ አፍ ከሆነው ደመወዝ ቀንሶ ቁጠባ መቆጠብ አልቻለም፡፡ በልዩ ልዩ እክሎች ምክንያት ሠራተኛዉ መደበኛ ሥራዉን ማከናወን ሳይችል ሲቀር ከሥራ መፈናቀልና የገቢ…